412ሺ 800 ብር በክረምቱ የደሀ ደሀ ተማሪዎች ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን 334 ተማሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ፦ አቶ አጽናኝ ፈለቀ

ሚዛን አማን ፣ ጥቅምት 1/2016 የቤንች ማጂ ልማት ማህበር የክረምቱ የደሀ ደሀ ተማሪዎች የሀብት አሰባሰብ ፕሮግራም መጠናቀቁን አስመልክቶ ዋና ስራ አስኪያጁ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አጽናኝ ፈለቀ ዛሬ በቢሮአቸው በሰጡት መግለጫ በ2016 የትምህርት ዘመን በዞኑ 400 የደሀ ደሀ ቤተሰብ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ በተደረገ የሀብት ማሰባሰብ ስራ 412ሺ 800 ብር በጥሬና በአይነት ሀብት መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ በመጀመሪያ ዙር 171 ደርዘን ደብተርና 37 ፓኮ እስክሪፕቶ ድጋፍ የተሰበሰበ ሲሆን በሁለተኛው ዙር 163 ደርዘን ደብተር ፣ 21 ፓኮ እስክሪፕቶና ለ10 ተማሪዎች ዩኒፎርም ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

በሁለቱ ዙር በአጠቃላይ 334 ደርዘን ደብተር ፣ 57 ፓኮ እስክሪፕቶና 10 ዩኒፎርም በድጋፍ የተገኘ ሲሆን በትምህርት ዘመኑ በዞኑ ከ9-12ኛ ክፍል በደረጃ ለወጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው 1ሺ ብርና የምስክር ወረቀት ማበረታቻ ልማት ማህበሩ መስጠቱን በመግለጫው ጠቁመዋል።

በደሀ ደሀ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለ334 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው 1 ደርዘን ደብተርና 5 ፍሬ እስክሪፕቶ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ወረዳዎችም ለታለመላቸው ተማሪዎች ማሰራጨታቸውን ክትትል አድርገናል ብለዋል።

ድጋፉ ከልማት ማህበሩ አባላት ፣ ከቅን ልባሞችና ከደጋፊዎች የተሰበሰበ መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀው ድጋፉን በማሰባሰብና በማስተባበር ለተሳተፉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ አጽናኝ በመጨረሻም የቤንች ማጂ ልማት ማህበር ላለፉት 27 ዓመታት በተለያዩ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና የሰብዓዊነት አገልግሎት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው ይህን ተግባር በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ገልጸዋል።

ወቅታዊና የተሟላ መረጃ ለማገኘት፦

በፌስ ቡክ፦https://www.facebook.benchmajidevelopmentassociation

ዌብ ሳይት ፦www.benchmajida.org.et

በኢንስታግራም፦https://www.instagram.com/p/CyAsM3ptHLa/?igshid=OGY3MTU3OGY1Mw==

ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው፡፡ እናመሰግናለን።

+13

All reactions:

11Tedy King, Yebelay Amene Yegeta and 9 others

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top