
ብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፣ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የልማት ማህበራችን የበላይ ጠባቂ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻ የ2016 አመታዊ የአባልነት ክፍያቸውን ፈጽመዋል።

ክቡር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ልማት ማህበሩን በቅርበት በመምራትና ገንቢ ሀሳቦችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ሲሆን በቅርቡ የመሰረተ ድንጋይ የሚቀመጥለትን የባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ የሀብት አሰባሳቢ አብይ ኮሚቴን በዋና ሰብሳቢነት እየመሩ ይገኛሉ።
ክቡር ዋና አስተዳዳሪና የልማት ማህበራችን የበላይ ጠባቂ ለዞኑ ነዋሪዎች ፣ አልሚ ባለሀብቶች ፣ ወጣቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና የንግዱ ማህበረሰብና ድርጅቶች የልማት ማህበሩ አባል በመሆን በጋራ ለህዝባችን እንስራ ብለዋል።
ነባርና አዲስ አባላትም በወቅቱ አመታዊ የአባልነት ክፍያችንን በተዘጋጁ የክፍያ አማራጮች በመፈጸም ማህበራዊና ሰብአዊ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
ክቡር ዋና አስተዳዳሪ በዞኑ ህዝብና በልማት ማህበሩ ስም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። በወጣ ይተካ ፣ ክፉ አይንካዎት ብለናል።
ክቡራንና ክቡራት ወደ ልማት ማህበሩ አዲስ አባል ለምትሆኑና ለነባር አባላት 1000023232007 የንግድ ባንክ አካውንት በመጠቀም ገቢ ማድረግና ስሊፑን ስክሪን ሹት አልያም ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም ገጻችን ብትልኩልን ደረሰኝና የልማት ማህበሩ መታወቂያ በማዘጋጀት የምንልክ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
ወቅታዊና የተሟላ መረጃ ለማገኘት፦
በፌስ ቡክ፦https://www.facebook.benchmajidevelopmentassociation
ዌብ ሳይት ፦www.benchmajida.org.et
በኢንስታግራም፦https://www.instagram.com/p/CyAsM3ptHLa/?igshid=OGY3MTU3OGY1Mw==
ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው፡፡ እናመሰግናለን።