የቤንች ማጂ ልማት ማህበር የልማትና የሰብአዊ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ይቻል ዘንድ በ2016 የአባላት መዋጮና ተሳትፎ ስራ ላይ በይፋ የንቅናቄ ስራ ጀምሯል።
በ2015 ዓመተ ምህረት በተቋማችን ማህበራዊ ሚዲያና የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም ባካሄድነው የቅስቀሳና የተሳትፎ ስራ በርካታ ነባርና አዲስ የልማት ማህበሩ አባላት አመታዊ መዋጮአቸውን በመክፈል አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል።
በዚህም የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ካቢኔዎች ፣ የጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና የመንግስት ሰራተኞች የልማት ማህበሩን ራዕይ ፣ አላማና ተልዕኮ በመረዳት የልማት ማህበሩ አባል በመሆን አዲሱን የልማት ማህበሩ መታወቂያ መውሰድ ችለዋል።
በወረዳዎች ፣ በክልልና በፌደራል ተቋማት ፣ በሚዛን አማን ፣ በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ያካባቢው ተወላጆች ፣ የልማት አጋሮችና ደጋፊዎች ካሉበት ሆነው የልማት ማህበራችን አጋርና አባል ሆነዋል።
በዞኑ የሚገኙ አልሚ ባለሀብቶች ፣ ወጣት ባለሀብቶች ፣ የግል የትምህርት ተቋማት ፣ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የግል የጤናው ሴክተሮች በባለቤቶቻቸውና በድርጅታቸው ስም አባል በመሆን የልማት ማህበሩ የጀርባ አጥንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በ2016 የልማት ማህበሩን አባላት ከከተማ እስከ ገጠር ፣ በቤተሰብ ፣ በግለሰብ ፣ በድርጅትና መሰል የአባልነት ዘርፎች ነባርና አዲስ አባላትን ወደ ማህበሩ በማቀላቀል ተደራሽነታችንን ለማስፋትና አገልግሎታችንን ለማጠናከር ያስችለን ዘንድ ስራችንን በይፋ መጀመራችንን እንገልጻለን።
ነባርና አዲስ አባላት ካሉበት ሆነው ለአባልነት መዋጮ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት 1000023232007 በማስገባት ደረሰኙን በቴሌግራም ስልክ ቁጥር 0908009830 ቢልኩልን ህጋዊ ደረሰኝ ቆርጠን የምናደርስላችሁ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን።
እንደ መሪ ቃላችን “ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው” በማለት እናንተን ውድ አባሎቻችንና አዲስ አባላትን በመያዝ ታላቅ የልማትና የሰብአዊነት ስራ ለመስራት ስንዘጋጅ እንደተለመደው ከጎናችን እንደምትሆኑ በመተማመን ነው።
ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው!!!
የቤንች ማጂ ልማት ማህበር
ወቅታዊና የተሟላ መረጃ ለማገኘት፦
በፌስ ቡክ፦https://www.facebook.benchmajidevelopmentassociation
ዌብ ሳይት ፦www.benchmajida.org.et
በኢንስታግራም፦https://www.instagram.com/p/CyAsM3ptHLa/?igshid=OGY3MTU3OGY1Mw==
ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው፡፡ እናመሰግናለን።