ቤንች ማጂ ልማት ማህበር በ2016 የትምህርት ዘመን 54 አዲስ ተማሪዎችን ወደ አዳሪ ትምህርት ቤቱ እንደሚያስገባ ገለጸ።

ሚዛን አማን ፣ ጥቅምት 1/2016 ልማት ማህበሩ ጥቅምት 3 (ቅዳሜ) በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ከአዲስ ተማሪዎች ወላጆች ጋር የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረም ገልጿል።

የልማት ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አጽናኝ ፈለቀ እንደተናገሩት ለ2016 ለአዳሪ ትምህርት ቤቱ አዲስ ተማሪዎች ቅድመ ምልመላ 104 ተማሪዎች የተለዩ ሲሆን 96 ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

የመግቢያ ፈተናውን ጨምሮ ለምልመላ የተዘጋጀውን ግልጽ መስፈርት ያሟሉ 52 ተማሪዎች እና 2 ተማሪዎች በቦርድ ልዩ ውሳኔ የገቡ ሲሆን በድምሩ 54 አዲስ ተማሪዎች በ2016 ወደ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ይቀላቀላሉ ብለዋል።

ውጤቱን ለሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተላከ ሲሆን በዚሁ መሰረት ጥቅምት 3 ማለትም የፊታችን ቅዳሜ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ግቢ የባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 03:00 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር በመገኘት የመግባቢያ ሰነድ የመፈራረም ስነ ስርዓት ይከናወናል ብለዋል።

በዕለቱ የሚመጡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ብርድ ልብስ ፣ አንሶላ ፣ መሸኛ ደብዳቤ ይዘው እንዲመጡ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው በልማት ማህበሩ በኩል የምግብ ፣ ውሃ ፣ መኝታና መሰል አስፈለጊ ጉዳዮች ዝግጅት አጠናቆ እየጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ የሚገቡ ተማሪዎች ከጥቅምት 05/2016 ጀምሮ መደበኛ ትምህርት የሚጀመር መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አጽናኝ ፈለቀ ገልጸዋል።

ወቅታዊና የተሟላ መረጃ ለማገኘት፦

በፌስ ቡክ፦https://www.facebook.benchmajidevelopmentassociation

ዌብ ሳይት ፦www.benchmajida.org.et

በኢንስታግራም፦https://www.instagram.com/p/CyAsM3ptHLa/?igshid=OGY3MTU3OGY1Mw==

ልማት የጋራ ጥረት ውጤት ነው፡፡ እናመሰግናለን።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top